About Us

አበሻ ክሪፕቶ በዘመናችን አዲስ ስለሆነና በፈጣን ሁኔታ የዓለምን ምጣኔ ሃብት ሁኔታ እየለወጠ ስላለው  ኪሪፕቶ ከረንሲ   እጅግ ውድና ብዙ ጥቅም የሚያገኙበትን መረጃ ያቀርብልዎታል፡፡ 

መረጃና እውቀት በሚገባ ለተጠቀሙበት ሰዎች እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

 የዚህ ድርጅት ባለቤት የሆንኩት እኔ ይህንን በተግባር አይቻለሁ፡፡ በፈረጆች አቆጣጠር በ2014 አካባቢ ስለ ቢት ኮይን በመስማቴ ወዲያኑ አሁን ከአርባ ሺህ በላይ የሚሸጠውን ቢትኮይን በአንድ መቶና ሁለት መቶ የመግዛት እድሉን አግኝቼ ነበር፡፡ ህዝባችን በዚያን ጊዜ ይህ መረጃ ቢኖረው ስንቶች ኖሮአቸው በተለወጠ ነበር ብየ አስባለሁ፡፡ ሆኖም አሁን ጊዚው አልረፈደም፡፡ ስለዚህ ይህን እውቀት አግኝተው ኑሮአቸውን መቀየር ለሚፈልጉ ሁሉ ትክክለኛውን መረጃ ለመስጠት እንፈልጋለን፡፡ ክሪፕቶ ከረንሲ ሁለት ገጽታ አለው፡፡ ትክክለኛ እውቀት አግኝተው ለሚሰሩ እጅግ ትርፋማ ሲሆን ብዙም እውቀት ሳይኖራቸው እንዲሁ ለሚሞክሩ ግን ገንዘባቸውን ሁሉ ሊያጡ የሚችሉበት እጅግ አደገኛም ነው፡፡ ስለሆነም አንዳንዱ እንደ እሳት ይፈራዋል አይነካውም አንዳንዱ ደግሞ ያለ እውቀት ገብቶ ገንዘቡን ያጣበታል፡፡ እነዚህ ወገኖች ሁለቱም ከስረዋል፡፡ አንደኛው በፍርሃት ተይዞ በእውቀት ገንዘቡን ኢንቨስት ባለማድረጉ ሊያገኝ የሚገባውን ትርፍ ሳያገኝ ባለበት ቀርቶአል ሌላኛው ደግሞ ያለ እውቀት ገብቶበት ገንዘቡን አጥቶአል፡፡ ትክክለኛው ግን በጊዜው እውቀቱን ካገኘ በኋላ ገንዘቡን በጥንቃቄ ኢንቨስት የሚያደርገው ሰው ነው፡፡ እናንተም እንደመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ሳትሆኑ እንደ ሶስተኛው ሰው በትክክለኛ እውቀት ታጥቃችሁ ገንዘባችሁን ለጥሩ ውጤት እንድትጠቀሙበት ልናበረታታችሁና የምንችለውን ሁሉ ልንረዳችሁ እንፈልጋለን፡፡ ለዚህም ዌብሳይታችንን እና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በመከታተል ተማሩ ለሌሎችም አሳውቋቸው፡፡ 

እናመሰግናለን 

ክሪፕቶ ማንኛውም ሰው በስልኩ ሊሰራው የሚችል ሲሆን ነገር ግን መሠረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ መሠረታዊ እውቀት አግኝታችሁ መጀመር ለምትፈልጉ ኢትዮጵያ ለምትኖሩ በነጻ በውጭ ለምትኖሩ ደግሞ በተመጣጣኝ ዋጋ ስልጠና እንሰጣለን፡፡

contact@abeshacrypto.com ብላችሁ አግኙን  

አበሻ ክሪፕቶ