Welcome to Abesha crypto

ወደ አበሻ ክሪፕቶ እንኳን በደህና መጡ፡፡

አበሻ ክሪፕቶ ምንድን ነው?


አበሻ ክሪፕቶ በአሜረካ ለሚኖሩ ሰዎች ብቻ እንደ Bitcoin Ethereum Dogecoin Shiba Inu እና የመሰሳሉ የተለያዩ ክሪፕቶዎችን መግዛትና በግል ቦርሳዎቸው ወይም wallet ማስቀመጥ ለሚፈልጉ ሰዎች እንዴት ገዝተው ማስተላለፍ እንደሚችሉ መሠረታዊ ስልጠና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ከቤትዎ ሳይወጡ በድህረ ገጽ ግንኙነት ብቻ በኮምፒውተርዎ ወይም በስልኮ እንዴት መግዛትና ማስተላለፍ እንደሚችሉ እናሳየዎታለን፡፡

ከፍተኛ ትርፍና ከፍተኛ ኪሳራ


ክሪፕቶ በዘመናች ገና እየተለመደ ያለ ዲጊጅታል ገንዘብ ሲሆን ነገር በጣም በጥንቃቄ አሰራሩን በሚገባ ተረድተን ልንገባበት የሚገባ ንግድ ነው፡፡ ብዙዎችን በአንድ ሌሊት ወይም በጥቂት ቀናት ቢልየነሮችና ሚሊየነሮች ያደረገ ቢሆንም እንደዚሁ በጥንቃቄ ያልገዙትንና ያልሸጡትን ደግሞ ያከሰረ ነገር ነው፡፡ ለዚህ እኔ ራሴ ምሳሌ ነኝ፡፡ ገና ቢትኮይን መሸጥ ሲጀምር አካውንት የከፈትኩበትና ኮይኑን የገዛሁበት ድርጅት አንድ ቢትኮይን እንደ እንኳን በደህና መጣህ ስጦታ በነጻ እንደሰጠኝ አስታውሳለሁ፡፡ በግዜው አንድ ቢትኮይን በሁለት መቶ ብር ሂሳብ አምስት ቢትኮይኖችን የገዛሁ ስሆን በጥቂት ጊዜ ስድስት መቶ ሲደርሱልኝ ብዙ ያተረፍኩ መስሎኝ ሁሉንም ሸጣቸዋለሁ፡፡ አምስት ዓመት ያህል ብጠብቅ እያንዳንዳቸውን በሰባ ሺህ ዶላር ሸጨ ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይሆኑልኝ ነበር ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ቢትኮይን በ2021 ሰባ ሺህ ዶላር የደረሰ ቢሆንም እንደገና ወርዶ አሁን አስራ ስድስት ሺህ ዶላር ላይ ነው፡፡ ስለዚህ የዲጂታል ኮይን ንግድ አትራፊና ወደፊትም የተለመደውን ገንዘብ እየተካ የሚሄድ ቢሆንም ትእግስትና ማስተዋልን የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ገበያ በቆየሁበት ጊዜ ከትርፌም ከኪሳራየም ከተማርኩት ትምህርት በመነሳት ወደገበያው አዲስ የምትገቡትን ልረዳችሁ ፈቃደኛ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይህን ግዙ ወይም አትግዙ ብለን ምክር መስጠት አንችልምም፡፡ ግዙልኝ ለሚሉም መግዛት አንችልም፡፡ ነገር ግን በራሳችሁ ወስናችሁ በዲጂታል ኮይን ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለምትፈልጉ እውቀቱ ለሌላችሁ እንዴት እንደምትገዙና እንዴት ዋሌት ከፍታችሁ የገዛችሁትን ማስተላለፍ እንደምትችሉ ደረጃ በደረጃ ልናሳያችሁ እንችላለን፡፡

ክፍያው ለአራት ሰዓት ሁለት መቶ ዶላር ብቻ ሲሆን አራቱን ሰዓት የግዴታ በአንድ ቀን መጠቀም አይኖርባችሁም፡፡ በተለያየ ቀን ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፡፡

የአገልግሎታችን ተጠቀሚ ለመሆን ስለመረጣችሁን እናመሰግናለን፡፡

በማንኛውም ሰዓት በTiktok መልክትዎን ሊልኩልን ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ ፦ በዚህ ዌብሳይት የሚቀርቡ መረጃዎች ሁሉ ለመረጃ ብቻ እንጂ ምንም አይነት ህጋዊ ምክሮች አይደሉም፡፡ ስለዚህ በገዛ ገንዘብዎ ውሳኔዎችን የሚያስተላልፉት እርስዎ ብቻ መሆኑዎን ይወቁ፡፡

Not financial Advice. All information on this website are for informatic only.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *